Windows 7 የቋንቋ በየነገፅ ፓኬት (ኤልአይፒ)
የ Windows 7 የቋንቋ በይነገፅ ፓኬት (ኤልአይፒ) በጣም በስፋት ጥቅም ላይ በዋሉ የ Windows 7 ስፍራዎች በከፊል አካባቢያዊ የሆነ የተጠቃሚ በይነገፅ ያቀርባል
ጠቃሚ! ከታች ቋንቋ ሲመርጡ ሙሉ የገጹ ይዘት ወደመረጡት ቋንቋ ይለወጣል።
ስሪት፡
1.0
የታተመበት ቀን፡
14/1/2011
የዶሴ ስም፡
LIP_am-ET-32bit.mlc
LIP_am-ET-64bit.mlc
የዶሴ መጠን፡
1.7 MB
2.5 MB
የ Windows የቋንቋ በይነገፅ ፓኬት (ኤልአይፒ) በከፊል የተተረጎሙ የ Windows ስሪቶችን በጣም በስፋት ጥቅም ላይ የሚውሉ ስፍራዎችን ያቀርባል። ኤልአይፒ ከተጫነ በኋላ በዊዛርድስ ውስጥ ያሉ ፅሑፎች፣ የዲያሎግ ሳጥኖች፣ ምናሌዎች እና የድጋፍ እና እርዳታ ርዕሶች በኤልአይፒ ቋንቋው ይታያሉ። ያልተተረጎመው ፅሑፍ በ Windows 7 የመሰረት ቋንቋ ይቀመጣል። ለምሳሌ የስፓኒሽ ቋንቋ ስሪት Windows 7 ገዝተው ከሆነ እና የካታሎኒያ ቋንቋ ከጫኑ፣ የተወሰኑ ፅሑፎች በስፓኒሽ እንደሆኑ ይቆያሉ። በአንድ ነጠላ የመሰረት ቋንቋ ላይ ከአንድ በላይ ኤልአይፒ መጫን ይችላሉ። Windows ኤልአይፒዎቸ በማንኛውም Windows 7 ምርቶች ላይ ሊጫኑ ይችላሉ።የሚደገፉ ስርዓተ ክንውኖች
Windows 7
• Microsoft Windows 7
• Windows 7 ተፈላጊ የመሰረት ቋንቋ ጭነት፡ እንግሊዘኛ
• 4.46 ሜጋ ባይት ለመገልበጥ ነፃ ስፍራ
• 15 ሜጋ ባይት ለማዋቀሪያ ነፃ ስፍራ
- ማስጠንቀቂያ፥ የነቃ BitLocker ምስጠራ ካለህ፣ እባክህን ኤል አይ ፒ (LIP)። ክፈት Control Panel፣ ምረጥ System and Security፣ ከዚያም BitLocker Drive Encryption። ጠቅ አድርግ በ Suspend Protection።
ለ Windows 7 ኤልአይፒ 32-ቢትእና 64-ቢት ስሪቶች የተያዩ መጫኛዎች በመኖራቸው ምክንያት፣ መጫንዎትን ከመጀመርዎ በፊት የትኛውን የ Windows 7 ስሪት እንደጫኑ መገመት ያስፈልግዎታል፡ የትኛውን የዊንዶውስ 7 ስሪት እንዴት እንደሚጭኑ ለመወሰን የሚከተለውን ይመልከቱ፡
ጠቅ አድርግ በ Start ቁልፍ እና ከዚያ በኮምፒዩተሩ ላይ ወደ ግራ ጠቅ ያድርጉ እና ይምረጡ Properties። ይህ ስለ አንተ ኮምፒዩተር መሰረታዊ መረጃ ያመጣል።
ለስርዓት አይነት በስርዓት ክፍል ውስጥ ተመልከት። ይህ የሚያሳየው የአንተ Windows 7 የክወና ስርዓት 32-ቢት የክወና ስርዓት ነው ወይም 64-ቢት የክወና ስርዓት ነው።
የ32-ቢት ስሪቱን ለመጫን ማድረግ የምትችለው:
- ጠቅ አድርግ አውርድአዝራርን፣ ከዛ ጠቅ አድርግOpenን LIPውን ለመጫን
- ጠቅ አድርግ የአውርድአዝራርን
- ላይ ጠቅ አድርግSave ፋይሉን ወደ ኮምፒዩተርህ ለመቅዳት፣
- LIPውን ለመጫን ወደ የወረደው ፋይል በመሄድ ሁለቴ ጠቅ አድርገው
ወይም
የ64-ቢት ስሪቱን ለመጫን፣ ከዚህ በላይ ያለው ሁለተኛ አማራጭን መጠቀም አለብህ።